Main Menu

ኦዲፒ ጥፋተኞቹን አሁንም በሥም መጥራት አልፈለገም

በምዕራብ ኢትዮጵያ የተከሰተውን አሳፋሪ ግዲያ ተከትሎ የኦዲፒ ማዕከላዊ ኮሚቴ ትላንት ባወጣው መግለጫ ደርግ ደርግ የሚሸቱ…. “በደም የተገኘን ድል በደም እንጠብቃለን”( እስከምናውቀው ደረስ ሕዝብ ነው የደማው፤ ኦሕዴድ በኢሕአዴግ ውስጥ ሆኖ ሕዝብን ያደማው)…..”የመቃብር አፋፍ”….”እንቀብራቸዋለን”…”እንሰባብራቸዋለን” የሚሉ አዳዲስ አደገኛ ቃላትን ከመደርደር ውጪ ጥፋተኞቹን አሁንም በሥም መጥራት አልፈለገም።

ይህ የተለመደ ኢሕአዴጋዊ ሽወዳ ነው። “የፀረ ሰላም ኃይሎች”…”የሻዓቢያ ተላላኪ ኃይሎች” ምናምን የሚሉ ቃላቶችን መጠቀም የተለመደ ነበረና። ምንም የተቀየረ ነገር የለም፤ ከሥሙ በስተቀር። የፕሮግራም፣ የርዕዮተ-ዓለም፣ የማኅበራዊ መሠረቱ…ምንም ለውጥ ሳይኖር cosmetic changes (ሥም፣ ሎጎ እና መዝሙሩን) ቀይረው በአዲስ መልክ ሌላ ኢሕአዴግ እየሆኑ ነው። ካድሬዎቻቸው ደግሞ ሲያቅለሸልሹ።

አብይ ወደ ሥልጣን ከመጣ በኋላ እንኳን በአሶሳ፣ በጋምቤላ፣ በራያ፣ በቡራዩ፣ በጌዲኦ፣ በሐዋሳ፣ በጉራጌ…..ጭፍጨፋዎች፣ መፈናቅሎች እና የንበረት ውድመቶች ተፈፅመዋል። ግን ይሄ ነው የሚባል የእርምት ሥራ አልተወሰደም። ወደፊትም እንደዚህ ዓይነት ነገሮች እንዳይደገሙ የተቀመጠ አቅጣጫ ግልፅ አይደለም።

የሚሠራው ተራ የሚዲያ ፍጆታ ቀለብ ነው። 22 የሠላም አምባሳደር ሴቶችን ወደ ትግራይ ክልል መላክ እንዴት ሰላምን ሊያረጋግጥ ይችላል? ትግራይ ክልል 22 ሴቶች የሚፈቱት የሠላም ችግር ምንድነው? በፖለቲካ ያልተግባቡት ቡድን መቀሌ እንዳለ እናውቃለን። ይሄንን የሚፈታው ግን ነጭ ባንዲራ የያዙ ሰዎች አይደለም። (በነገራችን ላይ ነጭ ባንዲራ ብዙ ጊዜ የምርኮኛ ባንዲራ ተደርጎ ነው የሚወሰደው)።

ከመግለጫው ግን ትኩረቴን የሳበው ነገር የመግለጫው አጠቃላይ መንፈስ ነው። ባዶ ወኔ የተሞላ ነው። በጣም በቀላሉ የሚያስበላቸው የፖለቲካ ስህተት ላሳያችሁ..

ልብ በሉ በሰብዓዊ መብት ጥሰት እና ከባድ መስና ወንጀሎች የተጠረጠሩትን በሕግ አግባብ መጠየቅ የሚችለው መንግሥት ነው እንጂ ፖርቲ አይደለም። ፓርቲ የራሱን የአስተዳደራዊ እርምጃ ሊውስድ እንጁ ማሰር አይችልም።

ኦዲፒ ግን ምን እንድሚል ስሙት….

“ፓርቲው እነዚህ አካላት ለህግ እንዲቀርቡ እንቅስቃሴ እያደረገ ባለበት ወቅት እነዚህ አካላት የሰሩት ጥፋት እንዲደበቅ አሊያም ህግን ለማስከበር የተጀመረው ስራ እንዲቋረጥ ለማድረግ በአጠቃላይ ወደ ነፃነት የተጀመረው ጉዞ እንዲደናቀፍ ሌት ተቀን እየሰሩ መሆኑን አስታውቋል”

በዚህ ዓረፍተ ነገር መሠረት ለሕግ የሚቀርበው ጥፋተኛ ማን ነው?
ለሕግ የሚያቀርበው አካልስ ማን ነው? ፓርቲ ነው ወይስ መንግሥት?

ከታሪክ ማስታወሻ

ደርግ ወደ ሥልጣን የመጣ ጊዜ የደርግ ማዕከላዊ ኮሚቴ (ሸንጎ) ንጉሠ ነገሥቱን ጨምሮ 60 የሚሆኑ የንጉሠ ነገስቱ ከፍተኛ ባለሥልጣናትን ያስረሸነው በፓርቲው ውሳኔ ነው።

ባጠቃላይ ድንፋታው አንድም አደገኛ ነው ሌላም ባዶ ቀረርቶ ነው።

የዛሬው የፕሬስ ሴክሬታሪያት ጥያቄ አመላለስ የሚነግረን ነገር ብዙ incoherence of the actions, complete lack of direction and priority እንዳለ ያሳያል። ለሚጠየቁ ጥያቄዎች አንድም አጥጋቢ መልስ አልተሰጠም። ቀጣይነቱን እጠራጠራለሁ። ቢልለኔ ካናዳዊ ዜግነቷን እንደምክንያት ተጠቅማ ላሽ በል የምትለው ይመስለኛል።

 

 

Mengistu Assefa

Mengistu Assefa

Dr. Mengistu Assefa is a dental surgeon by training. He writes commentaries, analyses and opinions pertaining to Ethiopian social, political and economic affairs. He can be reached at servezking@gmail.com
Spread the news
  • 308
    Shares


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked as *