Main Menu

ዶ/ር አብይ አህመድ – በጡረታ ከተገለሉ የቀድሞ ባለስልጣናት መሀከል ብዙዎቹ አኩርፈዋል

ዶ/ር አብይ አህመድ

ጠቅላይ ሚኒስቴሩ ዶ/ር አብይ አህመድ ትናንት በቤተ መንግስት ለትግራይ ተወላጅ ፣ ሽማግሌዎች፣ ፖለቲከኞች፣ ታዋቂ ሰዎች፣ አርቲስቶች፣ ባለ ሀብቶች፣ ወጣቶች እና ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች ከምሽቱ 12:00 ሰዓት ጀምሮ ባደረጉት ግብዣ እና ውይይት ላይ ከተናገሩት እና ብዙ ታዳሚዎቹን ያስገረሙ ንግግሮች ይዘን ቀርበናል

ዶ/ር አብይ “አንዳርጋቸው ፅጌን በማሰራችን የተጠቀምነው ነገር የለም” በማለት በቅርብ እንደሚፈታ ቃል ገብቷል፡፡ ይህንንም በእስር ላይ የሚገኘው አንዳርጋቸው ፅጌ እንዲያውቀው ተደርጏል፡፡ ዶ/ር አብይ “አንዳርጋቸው ፅጌን አስረን የተጠቀምነው ምንም ነገር የለም። ይልቁንስ ያተረፍነው ጥላቻ እና ከእንግሊዝ መንግስት 11 ቢሊየን ዶላር ማጣታችን ብቻ ነው” ማለታቸውን በስፍራው የነበሩ ሰዋች ለባቲ ፓስት ገልፀዋል፡፡ ከነዚህም መሀከል አቶአንዳርጋቸዉ ፅጌ መፈታት ላይ ከከፍኛ ባለሥልጣናት ጋር ይፈታ አይፈታ በሚል ጭቅጭቆች እንዳሉም አልሸሸጉም። እኔ የምለዉ የሱ መታሰር ጥቅሙ ምንድነው? አይፈታ የሚሉ ባለሥልጣናት አሉ ነገር ግን የገደለም እየተፈታ ነው። አስር ሰዉ የገደለውም ከረኔል ደመቀም ተፈቷል ብለዋል።።

ዶ/ር አብይ አህመድ በሚቀጥለው ሳምንት ወደ ግብፅ ተጉዘው በሊቢያ ታስረው በግብፅ የተቀበሩ ኢትዮጵያውያንን አስከሬን ይዤ አመለሳለሁ ብለዋል። አክለውም “ሰዎች እንደ እብድ ቢያዩኝም ይህን ማድረግ አለብኝ” ብለዋል።

ለምሳሌ ሸሬን አዉቃለሁ መቀሌ ብትሄድ የዉሃ ችግር አለ የተወሰኑ ለሆዳቸዉ ያደሩ ባለሥልጣናት በትግራይ ህዝብ የሚነግድ አሉ ብለዋል። ስልጣን ልቀቁ ሲባሉ ሞት የሚመስላቸዉ እና ሰሞኑን ጡረተ እንዲወጡ ከተደረጉት ባለሥልጣናት ዉስጥ ከአቶ ታደሰ ሀይሌ በስተቀር ብዙዎቹ ማኩርፉቸውን ገልፀዋል፡፡ ሁሉንም የግል ሥራ እንዲያገኙ እያደረግን ነዉ። ስልጣን በቃቹ እኔ እያለሁ አትጠየቁም አትታሰሩ ብዬ ነግሬቸዋለሁ እስኪ ገለል በሉ ኩርፌያ እና ጥላቻ ይቅር ብያለው። የመንግስት ባለሥልጣናት እና ሚኒስትሮች ይገመገማሉ ። አንዳንዶቹ 20ዓመት ሌላዉ 15አመት ቦሃላም ለተተኪው ቦታዉ መስጠት አይወዱም። ይህን በህገ መንግስት ማሻሻል አስተካክላለሁ። እኔ ባለሁበት ጊዜ አስተካክዬ ሌላዉ ምሳሌ ሆኜ በተርሜ መዉረድን ነዉ የምፈልገው ብለዋል። ኢህያዴግ ከኢትዮጲያ በታች ነዉ። እናንተ አታዉቁም እንጂ ብዙ ችግሮች በድርጅታች ውስጥ አለ። እሱን ለመቅረፍ እየሰራን ነዉ። የኦሮሞ አባገዳዎች ለዉጥ እያመጡ ነዉ ።አማራ ክልልም እየሰራን ነዉ። ትግራይም ስራ ልትሰሩ ይገባል።

ሰሞኑን የኤርትራዉን መሪ ኢሳያስ አፍወርቂን ለማግኘት በሳዉዳረቢያ ሸምጋኝነት የሣዉዲዉ ንጉስ ደዉለዉ ኘሬዛዳንቱ ጥሪያቸውን አንዳልመለሱ ተናግረው ጥረታቸውንም እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል፡፡ በሳዉዲ በነበረን ቆይታ የጠየቅናቸዉ ጥያቄዎች 10 ነበሩ። ከነሱ ውስጥም ዘጠኙ ሙሉ በሙሉ ተመለሰዎል አንድ ጥያቄ ብቻ በይደር እንደሚፈታ ተናግረዉ። የኤርትራዉ ኘሬዘዳንት ኢሳያስ አፍወርቅ ኢትዮጲያና ሱዳን መንግስቴን ለመጣል አሲረዋል ብለው ከሰውናል። እኛ ግን በሰለም ጉዳይ እና በልማት ላይ ነዉ ከኘሬዘዳንቱ አልበሸር ጋር የተወያየነዉ።

በመጭረሻም “በብሄራችሁ ለየብቻ የምጠራችሁ በአንድ ከመሰባሰባችን በፊት በተናጠል ቅድመ ህክምና መስራት ስላለብኝ ነው” ብለዋል። ክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር ሁሉንም ጥያቄዎች በትግስት ተቀብለዉ መልሰ ሰጥተዋል ።

Spread the news
  • 258
    Shares


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked as *