Main Menu

የማትናደፍ ንብ ከፈለክ ከዝንብ ጋር ተጋባ 

የማትናደፍ ንብ ከፈለክ ከዝንብ ጋር ተጋባ

? ትዳር ከንብ ጋር መኖር ነው። ለማሩ ስንል ንድፊያውን መታገሥ፡፡ ቆይተህ ደግሞ ንድፊያውን መልመድ፡፡ ገበሬ ቀፎ ሰቅሎ ንብ ሲያንብ ፣ ንብ እንደምትናደፍ ሳያውቅ ቀርቶ አይደለም፡፡ የማትናደፍ ንብ ከፈለገ በየደጁ ቆሻሻ ፍለጋ የምትጓዘው ዝንብ ነበረችለት፡፡ ዝንብ ምን ጠባይዋ ሸጋ ቢሆን ፤ ጠብ የሚላት ግን ሌላ ነገር ነው ፡፡

? ይህን ያውቃል ገበሬው፡፡ እያወቀም ንብ ያንባል፡፡ ማነብ ብቻ ሳይሆን ከንብ ጋር እንዴት መኖር እንደሚቻልም ያውቃል፡፡ ንብ ትናደፋለች ፤ ግን እንዳትናደፍ ማድረግም ይችላል፡፡ የምትወደውና የማትወደው ሽታ አለ፡፡ ስትቀርብህ ምን ማድረግና ምን አለማድረግ እንዳለብህ ገበሬው ያውቃል፡፡

? በሀገራችን ንብ አትገደልም፡፡ ነውር ነው፡፡ ብትነድፍም አትገደልም፡፡ የንቧን ማር ለመውሰድም ንቧን ገድሎ ፣ አጥፍቶ ፣ ጎድቶ ወይም አሰቃይቶ ሳይሆን በጭስ ራሱን እየተከላከለ ፣ ፊቱን በጨርቅ ሸፍኖ ፣ ወደ ንቧ ቀፎ ገብቶ ነው ማሩን የሚቆርጠው ፡፡ ንቧም ሳትጎዳ ፣ ማሩም ሳይጠፋ ፣ እርሷም ሳትናደፍ ፡፡

? ትዳርም እንዲህ ነው፡፡ አኗኗሩን ነው ማወቅ ፤ የንቧን ንድፊያ የመቀነሻውን መንገድ ነው ማወቅ፣ የማሩን አቆራረጥ መንገድ ነው ማወቅ፡፡ ደግሞም‘ኮ አስገራሚው ገበሬው የሚንከባከበው ይህቺኑ የምትናደፈውን ንብ መሆኑ ነው፡፡ የምትቀስመው አበባ ትፈልጋለች፣ ንጹሕ አካባቢ ትፈልጋለች፣ ከጉንዳንና ከአውሬ ነጻ የሆነ ቀፎ ትፈልጋለች፡፡ ግን ትናደፋለች፡፡ ደግሞም ማር ትሰጣለች ፡፡

? ትዳር አስደሳች ነገር ብቻ ሳይሆን አስመራሪ፣ አስጠሊታ፣ ጨጓራ አንዳጅ ፣ ልብ አቃጣይም ክፍል አለው፡፡ ይናደፋል፡፡ ግን ደግሞ እንክብካቤም ይፈልጋል ፡፡ ንጹሕ ልብ፣ ታማኝ ኅሊና ፣ ቻይ አንጀት ፣ ታጋሽ ሆድ ፣ ጠቢብ አእምሮ ፣ አሳላፊ ልቡና ይፈልጋል። ለምን ቢሉ ? ማር ይሰጣልና ታገሱ።

? ፌስቡክን (Facebook) ለመታወቅ ሳይሆን ያወቅነውን ለማሳወቅ እንጠቀም፡፡ ማወቅ መልካም ነው፡፡ ያወቁትን ማሳወቅ ደግሞ ፍፁም በጎነት ነው፡፡ በምድር ላይ የምናደርጋቸው ነገሮች ሁሉ በሰማይ ላይ የዘላለም ደመወዝ ሆነው ይከፈሉናል፡፡ ሁሌም ቢሆን ከክፋት ይልቅ በጎ በጎውን ነገር እናስብ መልካምነት ለራስ ነውና ፡፡

? ስለዚህ አንተም ይህ አሁን ያነበብከው መጣጥፍ ትምህርት ሰጪ ሆኖ ካገኘሀው የእርስዎ ዘመዶችህ እንዲያነቡትና ትምህርት እንዲወስዱ ዘንድ ሼር ያድርጉላቸው ።
.

Spread the news
  • 4K
    Shares


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked as *